በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ፒያሳ” - ለጥብቅ ከተማነት መስፈርቱን እንደማያሟላ የቅርስ ባለሥልጣኑ አስታወቀ


“ፒያሳ” - ለጥብቅ ከተማነት መስፈርቱን እንደማያሟላ የቅርስ ባለሥልጣኑ አስታወቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:30 0:00

የአዲስ አበባ ከተማ እንብርት የኾነውን ፒያሳን፣ በጥብቅ ከተማነት ለመከለል መስፈርቱን እንደማያሟላ፣ የኢትዮጵያ ቅርስ ባለሥልጣን አስታውቋል።

የተቋሙ ዋና ዲሬክተር አቶ አበባው አያሌው፣ ዛሬ ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የፒያሳ ገጽታ አካባቢውን በጥብቅ ከልሎ ለመጠበቅ የሚመች አይደለም፤ ብለዋል።

በፒያሳ እና በሌሎችም የከተማዋ አካባቢዎች፣ አሁን እየተከናወነ ባለው የመንገድ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት እየፈረሱ ያሉት ሕንፃዎች፣ በ2015 ዓ.ም ተሻሽሎ በጸደቀው መመሪያ መሠረት እየተከናወነ መኾኑንም ዋና ዲሬክተሩ አመልክተዋል።

ከዚህ ቀደም ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ባለሞያዎች ግን፣ በሥራ ላይ ያለው መመሪያ ውይይት እንዳልተደረገበት ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG