በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት ልዑካን በአዲስ አበባ ያደረጉት ቆይታ ካለስምምነት አበቃ


የዓለም አቀፍ ገንዘብ ድርጅት ልዑካን በአዲስ አበባ ያደረጉት ቆይታ ካለስምምነት አበቃ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:17 0:00

ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ለኢኮኖሚ መርሐ ግብሯ ድጋፍ እንዲያደርግላት ኢትዮጵያ ባቀረበችው ጥያቄ ላይ ለመነጋገር በአዲስ አበባ ያደረጉት ቆይታ ትላንት ማክሰኞ ካለ ስምምነት ተጠናቅቋል፡፡

ሮይተርስ በዘገባው እንዳመለከተው የዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት ልዑካን ጉዞ ስምምነት ሳይቋጭ ማብቃቱ ኢትዮጵያ ለዓለም አቀፍ አበዳሪዎች መክፈል ላለባት የብድር ዕዳ ክፍያ የሚውል ገንዘብ እንዲያጥራት ያደርጋል።

አይ ኤም ኤፍ እንዳስታወቀው በአዲስ አበባ ውይይት ሲያደርጉ የቆዩት ልዑካኑ ተቋሙ የኢትዮጵያ መንግሥትን የምጣኔ ሐብት መርሐ ግብር መደገፍ የሚችልበትን መንገድ ለመወሰን ጠቀም ያለ አዎንታዊ ውይይት አድርገዋል። ውይይቱ በዚህ በያዝነው እአአ ሚያዚያ ወር በዋሽንግተን እንደሚቀጥልም አመልክቷል፡፡

ቀደም ሲል ቻይናን የማይጨምረው የበለጸጉት አበዳሪ ሀገራት ስብስብ ዘ ፓሪስ ክለብ፤ “ኢትዮጵያ እስካለፈው መጋቢት 31 ቀን ድረስ ከኤይኤምኤፍ ብድር የማታገኝ ከሆነ የብድር ዕዳዎቿን እስከሚመጣው እአአ 2025 ዓም መክፈል እንዳይኖርባት የሰጠናትን እፎይታ እንሰርዛለን” ሲል ማስታወቁ የሚታወስ ነው፡፡ ሆኖም አበዳሪዎቹ ሀገሮች የጊዜ ገደቡ ባለፈው ዕሁድ ማለፉን ተከትሎ ውሳኔያቸውን ተግባራዊ ያደርጉት እንደሆነ ግልጽ አይደለም፡፡ ኢትዮጵያ ባለፈው 2023 ዓመተ ምሕረት ከቻይና ጋር የብድር ዕዳ ክፍያ እፎይታ ስምምነት ላይ መድረሷ ይታወሳል፡፡

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት አይኤምኤፍ ጋር የነበራት የኋለኛው የብድር ስምምነት እአአ በ2022 መጨረሻ ካበቃ ወዲህ ከተቋሙ የፋይናንስ ድጋፍ አግኝታ አታውቅም፡፡

ኢትዮጵያ ባለፈው ታህሳስ ለአንድ ቢሊዮን ዶላሩ የዩሮቦንድ የሚጠበቅባትን ክፍያ ሳትፈጽም የቀረች ሲሆን ይህም የቦንድ ክፍያዋን ያላጠናቀቀች ሦስተኛ የአፍሪካ ሀገር አድርጓታል፡፡

ለሁለት ዓመታት የዘለቀውን ጦርነት በሰላም ስምምነት ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያ ኢኮኖሚዋ በከፍተኛ የዋጋ ግሽበት፡ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት እና በውጭ ዕዳ ክፍያ መደራረብ እየተፈተነ ነው፡፡ የመንግሥት አሃዛዊ መረጃዎችን የጠቀሰው የሮይተር ዘገባ እንዳመለከተው ሀገሪቱ ያለባት የውጭ ብድር ዕዳ 28 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል፡፡ ይህም ለ1 ቢሊዮን ዶላር ቦንድ በዚህ የፈረንጆች 2024 ዓመተ ምሕረት መጨረሻ ታህሳስ ወር ላይ መከፈል ያለበትን ይጨምራል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG