ኢትዮጵያ ሄፐታይተስ ቢ እና ሄፐታይተስ ሲ በተሰኙት የጉበት በሽታ ተጠቂዎች አሃዝ ከሰሃራ በስተደቡብ ካሉ የአፍሪካ ሀገራት በሁለተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ። ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ይኸን አሃዝ የሚሸከም የጤና ስርዓትም ሆነ የላቀ ህክምና የላትም።
በዚህ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ለማምጣት ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ዶ/ር ቅድስት ኪዳኔ ይማም በሰሜን ካሊፎርኒያ ያሉ ባልደረቦቻቸውን በማስተባበር በቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሆስፒታል የተሻሻለ እና ጉበት ንቅለ ተከላ ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶች መስጠት የሚያስችል የህክምና ክፍል ለመመስረት የሙያ ስልጠናዎች እና የቁሳቁስ ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
ኤደን ገረመው ዶ/ር ቅድስትን እና የቅዱስ ጳውሎስ ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ባልደረባን አነጋግራ ተከታዩን አሰናድታለች።
መድረክ / ፎረም