በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል ጥቃቷን ስትቀጥል፣ ኔታንያሁ ቀዶ ጥገና ተደረገላቸው


ፍልስጤማውያንና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በጊዜያዊ መጠለያ ላይ የደረሰውን ጉዳት በመመልከት ላይ (ፎቶ ኤፒ መጋቢት 31፣ 2024)
ፍልስጤማውያንና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በጊዜያዊ መጠለያ ላይ የደረሰውን ጉዳት በመመልከት ላይ (ፎቶ ኤፒ መጋቢት 31፣ 2024)

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል የተኩስ አቁም ለማምጣት ካይሮ ላይ ጥረት በቀጠለበት ወቅት፣ እስራኤል በማዕከላዊ ጋዛ በአል አስቃ ሆስፒታል ውስጥ የነበሩ በርካታ መጠለያዎችን ደብድባለች፡፡ በጥቃቱ ሁለት ሰዎች እንደሞቱ ታውቋል። በሁለቱ ወገኖች ጦርነት መፈንዳቱን ተከትሎ፣ በአካባቢው በሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው ተጠልለው ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ለገጠማቸው የአንጀት መውረድ የቀዶ ጥገና ተደርጎላቸዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማደንዘዣ እስኪወጡም፣ የፍትህ ሚኒስትር የሆኑትና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ሥልጣን የያዙት፣ የኔታንያሁ የቅርብ ሰው ያሪቭ ሌቪን የጠቅላይ ሚኒስትር ሥልጣኑን ለጊዜው ይዘዋል።

ሐማስ፤ ያገታቸውን ሰዎች ለመልቀቅ፣ የተኩስ አቁም እንዲደረግና እስራኤል ከጋዛ እንድትወጣ እንዲሁም ፍልስጤማውያን እስረኞች እንዲልቀቁ ቢጠይቅም፣ ሜንጃሚን ኔታንያሁ አይቀበሉም።

ሐማስ ሙሉ ለሙሉ እስከሚጠፋ ድረስ ውጊያውን እንደሚቀጥሉ ኔታንያሁ በተደጋጋሚ አስታውቀዋል።

ጋዛ በአብዛኛው የወደመች ሲሆን አብዛኛው ነዋሪዋም በደቡባዊ የሰርጡ ክፍል ተጠልሎ ይገኛል።

በእስራኤል ጥቃት እስከ አሁን ከ32 ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን እንደተገደሉ የራስ ገዙ የጤና ሚኒስቴር ያስታውቃል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG