የሮማው ካቶሊክ ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ ዛሬ የተከበረውን የፈረንጆች ፋሲካ ሃይማኖታዊ ሥነ ስርዓት ለመምራት በቫቲካን ከተማ በሚገኘው የቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገኝተው ቡራኬ ሰጥተዋል።
አቡኑ 87 ዓመታቸው ሲሆን፣ የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ ሆኖ ከርሟል። የዛሬውን ቡራኬ የሰጡትም በተንቀሳቃሽ ወንበር ላይ በመሆን ነው።
ዓርብ በስቅለት ላይ በነበረ ሥነ ስርዓት እንደማይገኙ በመጨረሻው ሰዓት ላይ በመታወቁ፣ የአቡኑ የጤና ሁኔታ አሳሳቢ ሆኖ ነበር። ለእሁዱ ሥነ ስርዓት እረፍት እንዲያገኙና ለጥንቃቄ ሲባል እንዳልተገኙ ቫቲካን በመግለጫ አስታውቆ ነበር።
አቡኑ ለከተማዋና ለዓለም ቡራኬያቸውን ሲያስተላልፉ፣ ሥነ ስርዓቱ በመላው ዓለም በቴሌቭዥን ተላልፏል። ከመላው ዓለም የመጡ 6ሺሕ የሚሆኑ ታዳሚዎች በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ተገኝተዋል። አቡኑ በመላው ዓለም ስለሚካሄዱ ግጭቶች አንስተው ተናግረዋል።
የጤና ሁኔታቸው ሥራቸውን የሚያውክ ከሆነ ቦታቸውን እንደሚለቁ አቡነ ፍራንሲስ ከዚህ በፊት አስታውቀው ነበር። ይህም ከእርሳቸው ቀደም ብለው የነበሩትን የአቡነ ቤኔዲክት አርአያ በመከተል እንደሆነ ተነግሯል። አቡኑ በዚህ ወር ባወጡት አንድ ማስታውሻ፣ ቦታቸውን ለመልቀቅ የሚያበቃ የሚያሳስብ ነገር እንደሌለ ጠቁመዋል።
ከ10 ዓመታት በፊት፣ እ.አ.አ 2013፣ አቡነ ቤኔዲክት በፈቃዳቸው ቦታቸውን በመልቀቅ በመካከለኛው ዘመን የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስ ሆነዋል።
መድረክ / ፎረም