በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፑንትላንድ የሶማሊያን ሕገ-መንግስታዊ ማሻሻያ ተቃወመች


የፑንትላንድ ፓርላማ (ፎቶ ፋይል፣ የካቲት 1፣ 2024 ፌስቡክ)
የፑንትላንድ ፓርላማ (ፎቶ ፋይል፣ የካቲት 1፣ 2024 ፌስቡክ)

የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ እንደሚከተል ማስታወቁን ተከትሎ፣ ራስ ገዟ ፑንትላንድ ለፌዴራል ተቋማት እውቅና እንደማትሰጥ አስታውቃለች።

ሞቃዲሹ ከሚገኘው ማዕከላዊ መንግስት ጋራ ያላትን ተቃውሞዎች በተደጋጋሚ በመግለጫ ስታስታውቅ የከረመችው ፑንትላንድ፣ ዛሬ እሁድ ባወጣችው መግለጫ፣ በትናንትናው ዕለት በርካታ ሕገ መንግስታዊ ማሻሻዮችን ያደረገው የሶማሊያ ፓርላማ ያሳለፈውን ውሳኔዎችም ውድቅ አድርጋለች።

“በጋራ መግባባት ላይ የሚደረስበት ሕገ መንግስታዊ ሂደት እስከሚፈጠር ድረስ የፑንትላንድ አስተዳደር ለፌዴራል ተቋማት እውቅና አይሰጥም፣ ተቋማቱ ላይም እምነት የለውም” ብሏል መግለጫው።

ሕዝበ ውሳኔ የሚደረግበት ሕገ መንግስት እስከሚወጣ ድረስ፣ ፑንትላንድ የራሷ መንግስታዊ ስልጣን እንደሚኖራትም አስታውቃለች፡፡

ውስብስብ የሆነውንና በጎሳ መሠረት የሚደረገውን ምርጫ ሶማሊያ ከአምሣ ዓመታት በላይ ስትጠቀምበት ቆይታለች፡፡

ትናንት የተሰበሰበው የሶማሊያ ፓርላማ ‘አንድ ሰው አንድ ድምጽ’ የሚለውን ዓለም አቀፍ የምርጫ መርህ ተግባራዊ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ተከትሎ፣ በፑንትላን የሚገኙ ባለሥልጣናት ቁጣቸውን ገልፀዋል።

በተፈጥሮ ሃብቶች እና በቦሳሶ ወደቧ በመተማመን፣ ፑንትላንድ በእ.አ.አ 1998 ራስ ገዝ መሆኗን አውጃለች፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG