በመጪው 47ኛ የአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ የሥነ ተዋልዶ መብት ትልቅ ስፍራ እንደሚኖረው ተጠቆመ። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ እ.አ.አ ኅዳር አምስት ቀን ለሚካሔደው ምርጫ በያዙት የምረጡኝ ዘመቻ፣ ለሴቶች ጤና እና ለሥነ ተዋልዶ መብቶቻቸው ቁልፍ ቦታ ሰጥተዋል።
የሪፐብሊካን ፓርቲ ተፎካካሪያቸው የቀድሞ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ ደግሞ፣ ፅንስ ማስወረድን አስመልክቶ ሲናገሩ ቢሰነብቱም፣ እስከ አሁን አቋማቸውን በግልጽ አላስቀመጡም።
የቪኦኤዋ ሎረል ቦውማን ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።