የኢሕአፓ ሊቀ መንበር ትላንት ማክሰኞ በቁጥጥር ሥር ሲውሉ፣ የፓርቲው ምክትል ሊቀ መንበር እና የትንሣኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር ደግሞ ከእስር ተለቀዋል፡፡
የኢሕአፓ ተቀዳሚ ምክትል ሊቀ መንበር መጋቤ ብሉይ አብርሃም ሃይማኖት፣ ከታሰሩበት የአዋሽ አርባ ወታደራዊ ማሠልጠኛ ካምፕ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ እንደተለቀቁ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ምክንያት በዚያው በአዋሽ አርባ ከታሰሩት ፖለቲከኞች መካከል፣ የትንሣኤ ሰባ እንደርታ ፓርቲ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ጊደና መድኅንም እንደተለቀቁ፣ የፓርቲው ሊቀ መንበር አቶ ከበደ አሰፋ አረጋግጠዋል፡፡
ትላንት ከታሰሩት የኢሕአፓ ሊቀ መንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ጋራ “የእርስ በእርስ ጦርነት ይብቃ” በሚል ተጠርቶ የነበረውን ሰልፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሌሎች ሁለት ፖለቲከኞችም በቁጥጥር ሥር ውለው ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።