በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በአማራ ክልል የጎብኝዎች ቁጥር በእጅጉ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ


በአማራ ክልል የጎብኝዎች ቁጥር በእጅጉ ማሽቆልቆሉ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:02 0:00

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የተዳከመው የአማራ ክልል ቱሪዝም፣ በክልሉ ውስጥ በቀጠለው የትጥቅ ግጭት ክፉኛ እየተጎዳ እንደሚገኝ፣ የክልሉ የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ።

የቢሮው ምክትል ኃላፊ ዶክተር አየለ አናውጤ ዛሬ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ከሰሜኑ የአገሪቱ ጦርነት በፊት፣ ከ270ሺሕ በላይ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ቁጥር ይመዘገብ እንደነበር አውስተዋል፤ ባለፉት ስድስት ወራት የተመዘገቡ የውጭ ሀገር ጎብኝዎች ብዛት ግን ከ10ሺሕ ያልበለጠ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡

በዚኽም ክልሉ በየዓመቱ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ገቢ እያጣ እንደኾነ ያመለከቱት ምክትል ቢሮ ኃላፊው፣ “የጸጥታ ችግሩ ሳይሻሻል ከቀጠለ፣ የክልሉ የቱሪስት መስሕቦች በጎብኝዎች የመረሳት ዕድላቸው ሰፊ ነው፤” ብለዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG