በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኅትመት ዋጋ እና የሳተላይት ክፍያ መናር


 የኅትመት ዋጋ እና የሳተላይት ክፍያ መናር
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:11 0:00

በኢትዮጵያ እየጨመረ በቀጠለው የኅትመት ዋጋ እና የሳተላይት ክፍያ ምክንያት የብዙኀን መገናኛ ተቋማት ችግር ላይ እንደወደቁ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኀን ምክር ቤት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታምራት ኀይሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ በዋጋ ንረቱ ምክንያት ሥራቸውን አቁመው ከገበያ የወጡ ብዙኀን መገናኛዎች መኖራቸውን አስታውቀዋል፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው የኅትመት ብዙኀን መገናኛ ባለቤቶችም፣ በኅትመት ዋጋ መናር የተነሣ ሥራ ማቆማቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብዙኀን መገናኛ ምክር ቤት በቅርቡ ባካሔደው ጉባኤ፣ ዘርፉን ስለገጠሙት ፈተናዎች መወያየቱን ያነሡት አቶ ታምራት፣ መንግሥት ለችግሩ ትኩረት እንዲሰጥ ጠይቀዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG