በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሚጣሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ክምችት ጨምሯል


ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 18፣ 2024)
ፎቶ ኤፒ (መጋቢት 18፣ 2024)

ልዩ ልዩ የኤሌክትሪክ እና የተጣሉ የኢሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች በዓለም ላይ ያለቅጥ እየተከማቹ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ዓለም አቀፍ የቴሊኮሙኒኬሽን ሕብረት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስልጠናና ምርምር ማዕከል ባወጡት አዲስ ጥናታዊ ዘገባ አስጠነቀቁ፡፡

ስጋት ሆነዋል የተባሉት “ኢ ዌስት”(ኢሌክትሮኒክ ቆሻሻ) የሚል መጠሪያ የተሰጣቸውና ከሶኬቶቻቸው ወይም ከባትሪዎቻቸው ጋር የሚጣሉ፣ እንደ ስልክ፣ ላፕቶፕ ወይም የኤሌክትሪክ መኪናዎች ከመሳሰሉት የሚወገዱ ቁሶችናቸው፡፡ በአዲሱ ሪፖርት መሠረት፣ እ አ አ በ2022 ወደ 62 ሚሊዮን ቶን የሚጠጋ ኢ-ቆሻሻ ወይም ውጋጅ የተመዘገበ ሲሆን ይህ አካሄድ እየተቀለበሰም ይሁን ቁሳቁሱን መልሶ የመጠቀም አዝማሚያ ስለመኖሩ የሚጠቁም ምልክት አለመታየቱ ተገልጿል፡፡

የተጣሉት መሣሪያዎች ሜርኩሪ ወይም ብዙም የማይገኙ የከርሰ ምድር ብረቶችን የመሳሰሉ አደገኛ ቁሶችን ሊይዙ እንደሚችሉም ተመልክቷል።

ከኤሌክትሮኒክስ እና ኤሌክትሪክ መሳሪያዎች የሚወገዱ ቆሻሻዎችም ብዙ ጊዜ በአግባቡ እንደማይቀመጡ ተገልጿል፡፡

እኤአ በ2022 ተጥለው የተከማቹትን የኤሊክትሮኒክስ መሣሪዎች መልሶና አድሶ ለመጠቀም የተደረገው ጥረት ከ22 ከመቶ ጥቂት እልፍ ያለ ብቻ መሆኑም ተጠቅሷል፡፡

የተጣሉ መሳሪያዎች መበራከታቸው ከፍተኛ ተጠቃሚነትንም ጭምር የሚያሳይ በመሆኑ፣ ውስን የጥገና አማራጮች ዕጥረት እና የመሳሪያዎች የአገልግሎት እድሜ አጭር መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል፡፡

ማህበረሰቡን ከፍተኛ የኤሌክትሮኒክስ ቁሶች ተጠቃሚ ማድረግ ቢኖርም፣ ከነዚህ ቁሶች የሚወገዱና የሚጣሉ ቁሳቁሶችን በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል በቂ መሠረተ ልማት አለመኖሩን የተባበሩት መንግሥታት ተቋማት ገልጸዋል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG