በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት አስመራ ናቸው


የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል
የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ፣ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል

የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሃሳን ሼክ የኤርትራ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ያቀረቡላቸውን ግብዣ ተቀብለው ለሁለት ቀን የሥራ ጉብኝት ዛሬ ከሰዓት አስመራ መግባታቸውን፣ የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በትዊተር ገፁ አስታወቀ።

ሚኒስቴር መስሪያቤቱ ኤክስ በተሰኘው ማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው የቪዲዮ መልዕክት፣ የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ወደ ኤርትራ የተጓዙት በሶማሊያ ስላለው እድገት እና መሻሻል ለኤርትራው አቻቸው ለመግለፅ እና ሶማሊያን ከአሸባሪዎች ነፃ ለማውጣት በሚደረገው ጥረት ምክራቸውን ለመጠየቅ መሆኑን ተናግረዋል።

"ኤርትራ በሀገር ግንባታ፣ በመንግሥት ግንባታ እና በፀጥታ ዘርፍ ግንባታ ጥሩ ልምድ አላት" ያሉት ሞሐመድ፣ በርካታ የሶማሊያ ወታደሮች በኤርትራ መሰልጠናቸውን እና ኤርትራ ብዙዎቹ የዓለም ሀገራት የማያደርጉትን ድጋፍ ለሶማሊያ ማድረጓን ገልፀዋል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል በተመሳሳይ ሁኔታ በኤክስ ላይ ባጋሩት መልዕክትም ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ ትብብር ግንኙነቶች እና በሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG