በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያው ምርጫ የፑቲንን ሥልጣን እንደሚያራዝም ተጠብቋል


በፓሪስ የፑቲንን ዳግመኛ ለምርጫ መቅረብ በመቃወም የተካሄደ ሰልፍ
በፓሪስ የፑቲንን ዳግመኛ ለምርጫ መቅረብ በመቃወም የተካሄደ ሰልፍ

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ምንም ዓይነት ተቃዋሚ በሌለበት የዛሬውን እሁድ ምርጫ በማሸነፍ የስልጣን ዘመናቸውን ለተጨማሪ ስድስት ዓመታት ያራዝማሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባለፈው የካቲት በሩሲያ እስር ቤት ውስጥ እያለ ህይወቱ ያለፈውን ታዋቂውን የሩሲያ ተቃዋሚ መሪ አሌክሲ ናልቫኒን ሞት ተከትሎ፣ አንዳንድ ሩሲያውያን በምርጫ ጣቢያዎች የተቃውሞ ሰልፎችን ቢያደርጉም የ71 ዓመቱ ፕሬዚዳንት ፑቲን አሸናፊነት የተረጋገጠ እንደሚሆን ተገምቷል፡፡

ፑቲንን የሚገዳደር ምንም ዓይነት የረባ ተቃዋሚ እጩ ሳይኖር ያለምንም ተቃናቃኝ ባላፈው ዓርብ የጀመረው ምርጫ ዛሬ እሁድ ተጠናቋል፡፡

ከፑቲን ለመፎካከር በምርጫው እንደነገሩ የቀረቡ ሶስት ተፎካካሪዎች ቢኖሩም ፑቲንን በመቃወም ወደ ተለያዩ የአገሪቱ ምርጫ ጣቢያዎች ያመሩ አንዳንድ ሩሲያውያን የተቃውሞ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡

በ14 የሩሲያ ከተሞች ከ50 በላይ የሚደርሱ ተቃዋሚዎች ዛሬ እሁድ መታሰራቸውም ተዘግቧል፡፡

በተለያዩ የዓለም ከተሞች በሚገኙ የሩሲያው ኤምባሲዎችም ተመሳሳይ የተቃውሞ ዝግጅቶች ተካሂደዋል፡፡

የአሌክሲ ናቫልኒ ባለቤት እኤአ መጋቢት 15 በቡዳፔስት በተካሄደው ሰልፍ ላይ ባስተላለፉት መልእክት "አሌክሲ ጥቃቅን የመሰሉ ነገሮች ማለትም የመናገር ነፃነት፣ ፍትሃዊ ምርጫ፣ ዲሞክራሲ እና ያለ ሙስና እና ጦርነት የመኖር መብታችን ናቸው" ሲል ተናግሯል ብለዋል፡፡ "ፑቲን ሩሲያ አይደለም ፣ ሩሲያ ፑቲን አይደለችም።” ሲሉም አክለዋል፡፡

ሶስተኛውን ዓመት እያስቆጠረ በሚገኘው የዩክሬን ጦርነት ከፍተኛ ተቃውሞ ቢቀሰቀስም ፕሬዚዳንት ፑቲን ጦርነቱን ለሩሲያ ህልውና ሲባል ከምዕራባውያን ጋር የሚደረግ ጦርነት አድርገው አቅርበውታል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG