በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፋኖ ታጣቂ የተያዙ ሠራተኞችን ለማስለቀቅ እየጣረ መሆኑን ቀጣሪ ኩባንያው ገለጸ


የአማራ ክልል አካባቢን የሚያሳይ ካርታ
የአማራ ክልል አካባቢን የሚያሳይ ካርታ

⇔ የፋኖ ታጣቂዎች በ72 ሰዓታት ውስጥ እንለቃቸዋለን ብለዋል

ለሕዳሴ ግድብ አካባቢ የደን ምንጣሮ፣ ከጋርዱላ እና አሌ ዞኖች የመለመላቸውና ለሥራው በጉዞ ላይ እያሉ በምሥራቅ ጎጃም ዞን በፋኖ ታጣቂዎች የተያዙ የቀን ሠራተኞችን ለማስለቀቅ ጥረት እያደረገ እንደኾነ፣ ቀጣሪ ኩባንያው አስታወቀ፡፡

የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ መኾናቸውን የገለጹት ፋኖ ማርሸት ፀሐዩ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃል ታጋቾቹን በ በሰባ ሁለት ሰዓታት ውስጥ ለቀይ መስቀል እንደሚያስረክቧቸው ገልፀዋል። የቀጣሪ ኩባንያው ኒኮትካ ኮንስትራክሽንና ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር የፕሮጀክት ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙሉጌታ አለነ፣ በታጣቂ ኀይሉ ተይዘው የተወሰዱት የቀን ሠራተኞች ቁጥር 272 እንደኾነም ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል፡፡

በተያያዘ፣ የታገቱት ሠራተኞች ወታደራዊ ሥልጠና እንዲወስዱና በውጊያ እንዲሳተፉ እየተገደዱና የግድያ ዛቻም እየደረሰባቸው እንደኾነ መስማታቸውን፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ባለፈው የካቲት 18 ቀን 2016 ዓ.ም. በመንግሥት እና ሕጋዊ እውቅና ባለው ተቋም ለሥራ ተመልምለው ሲጓዙ ለታገቱ ወጣቶች ጉዳይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልልም ኾነ የፌዴራሉ መንግሥት ተገቢ ትኩረት መንፈጋቸውን የጠቀሱት ቤተሰቦቻቸው፣ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች ተቋማትም ዝምታ መምረጣቸው እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሠራተኞች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮን፣ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንን አስተያየት ለማካተት ያደረግነው ሙከራ፣ ኃላፊዎቹ ስልካቸውን ስለማያነሡ አልተሳካም፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ይከታተሉ።

በፋኖ ታጣቂ የተያዙ ሠራተኞችን ለማስለቀቅ እየጣረ መሆኑን ቀጣሪ ኩባንያው ገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:17:06 0:00

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG