በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ባለሥልጣን ወደ ኢትዮጵያና ቻድ ይጓዛሉ


በዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የፍልሰተኞች እና የስደተኞች ረዳት ጸሐፊ ሁሊዬታ ቫልስ ኖይስ።
በዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የፍልሰተኞች እና የስደተኞች ረዳት ጸሐፊ ሁሊዬታ ቫልስ ኖይስ።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር የሕዝብ፣ የፍልሰተኞች እና የስደተኞች ረዳት ጸሐፊ ሁሊዬታ ቫልስ ኖይስ በመጪው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያና ቻድ እንደሚጓዙ ከውጪ ጉዳይ መ/ቤቱ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።

ረዳት ጸሐፊዋ በሁለቱም ሀገራት ካሉ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት፣ የዓለም አቀፍ ድርጅት ተቋማት፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች፣ እንዲሁም ከአሜሪካ አጋሮች ጋራ ፍልሰተኞችን ስለማስፈር፣ የሰብአዊ ሠራተኞችን ከአደጋ ስለሚጠበቁበት እንዲሁም ባለፈው ዓመት በዓለም አቀፍ የፍልሰተኞች መድረክ ላይ የተገቡት ቃሉችን በተመለከተ እንደሚነጋገሩ ይጠበቃል። በተለይ በቻድ ጉብኝታቸው ደግሞ በአገሪቱ ላለው የሰብአዊ ሁኔታም ሆነ በሱዳን ለሚታየው ቀውስ በቻድ መንግት እና ዓለም አቀፍ ተቋማት በተሰጠው ምላሽና ላይ እንደሚያተኩሩ ታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG