በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ


የአዲስ አበባ-ደሴ መንገድ መዘጋት የከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጫና ማሳደሩ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:13 0:00

ከአዲስ አበባ በደብረ ብርሃን መንገድ በኩል ወደ ደሴ የሚደረገው የየብስ ትራንስፖርት መቋረጡ ለከፋ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጽእኖ ዳርጎናል፤ ሲሉ፣ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡ የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር እና የሰሜን ሸዋ ዞኖች ነዋሪዎች አስታወቁ፡፡

አስተያየት ሰጭዎቹ፥ ሕክምና ለማግኘት ተቸግረናል፤ የሸቀጥ ዋጋ ከዕጥፍ በላይ ጨምሯል፤ አርሶ አደሩ ያመረተውን ምርት ወደ ገበያ ለማቅረብ አልቻለም፤ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰንበቴ ከተማ አካባቢ፣ ሕክምና መውሰድ የነበረባቸው አምስት እናቶች መንገዱ ስለተዘጋ በወሊድ ምክንያት እንደሞቱ፣ የከተማው ጤና ጣቢያ አመልክቷል፡፡

በተመሳሳይ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ከአጣዬ ከተማ አካባቢ፣ ለተሻለ ሕክምና በሌላ መንገድ በመወሰድ ላይ የነበረ አንድ ሕፃን፣ ወደ ሕክምና ተቋም ሳይደርስ ሕይወቱ እንዳለፈ፣ አንድ የጤና ባለሞያ ጠቁመዋል፡፡

ሌላው የአጣዬ ከተማ ነዋሪም፣ ቀደም ሲል ከተማዋ ከ10 ለማያንስ ጊዜ ቃጠሎ እንደተፈጸመባት አውስተው፣ ከዚያ ጥፋት ሳታገግም ለሌላ ጉዳት ተዳርጋለች፤ ብለዋል፡፡

የሁለቱ ሃይማኖቶች አጽዋማት እየተፈጸሙ ባለበት ወቅት መንገዱ መዘጋቱ ደግሞ፣ የሸቀጥ አቅርቦት እጥረቱ እንዲባባስ ማድረጉን፣ አስተያየት ሰጭዎቹ አስረድተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG