በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሣ


ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሣ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:23 0:00

ምክር ቤቱ የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሣ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ኀሙስ፣ መጋቢት 5 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ፣ ሰባት ወራት በእስር ላይ የሚገኙትን የአባሉን የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት አነሣ።

አቶ ክርስቲያን፣ እስከ አሁን ምንም ዓይነት ክስ ሳይቀርብባቸው በእስር ላይ እንደሚገኙ፣ ጠበቃቸው አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ ተናግረዋል፡፡

ምክር ቤቱ በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ውስጥ ኾኖ ያለመከሰስ መብታቸውን ካነሣ፣ ለምን እስከ አሁን እንደዘገየ ግልጽ አይደለም፤ ሲሉ ጠበቃው ለአሜሪካ ድምፅ አመልክተዋል፡፡

በአማራ ክልል የተፈጠረውን የጸጥታ መደፍረስ ተከትሎ፣ ባለፈው ዓመት ነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. በተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ የታሰሩት የአቶ ክርስቲያን ታደለ ያለመከሰስ መብት በምክር ቤቱ የተነሣው፣ ከሰባት ወራት ቆይታ በኋላ ነው፡፡

ይህን አስመልክቶ፣ የፍትሕ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ፣ ለምክር ቤቱ በሰጡትና በሀገር ውስጥ ብዙኀን መገናኛዎች

በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢም የነበሩትን አቶ ክርስቲያን ታደለን አስመልክቶ የቀረበውን ያለመከሰስ መብትን የማንሣት ጥያቄ፣ በሁለት ድምፀ ተዓቅቦ እና በሁለት ተቃውሞ በአብላጫ ድምፅ መጽደቁ ተገልጿል፡፡

የአቶ ክርስቲያን ታደለ ጠበቃ እና የሕግ አማካሪ አቶ ሰሎሞን ገዛኸኝ፣ ደንበኛቸውን እስከ አሁን በአካል እንዳላገኟቸው ገልጸው፣ ያለመከሰስ መብታቸው መነሣትንም ከብዙኀን መገናኛዎች መስማታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ተወካይ የኾኑት አቶ ክርስቲያን ታደለ፣ የምክር ቤቱ አባል የኾኑት በስድስተኛው አገራዊ ምርጫ፣ ከአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል ተወዳድረው በመመረጣቸው ነው፡፡

በአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ የታሰሩትና ቀደም ብሎ ያለመከሰስ መብታቸው የተነሣው የአማራ ክልል እና የአዲስ አበባ ምክር ቤቶች አባላት አቶ ዮሐንስ ቧያለው እና ዶክተር ካሳ ተሻገር እንደቅደም ተከተላቸው፣ እስከ አሁን ክስ እንዳልተመሠረተባቸው ጠበቃቸው ተናገረዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት ያለመከሰስ መብት፣ የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጁ በሥራ ላይ እያለ ከተነሣ፣ እስከ አሁን ለምን እንደዘገየም ግልጽ አይደለም፤ ሲሉ አቶ ሰሎሞን ይጠይቃሉ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት፣ “መንግሥትን ለመጣል ከሽብር ቡድኖች ጋራ በኅቡእ ያሴራሉ፤” በሚል በእስር ላይ የሚገኙትን የቀድሞ የሰላም ሚኒስትር ደ’ኤታ የአቶ ታዬ ደንደኣን ያለመከሰስ መብት፣ ባለፈው የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ማንሣቱ ይታወሳል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG