በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፓስፖርት ፈላጊዎች ጉዳይ


የፓስፖርት ፈላጊዎች ጉዳይ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:35 0:00

በመንፈቅ ዓመት ውስጥ ከ640ሺሕ በላይ ፓስፖርቶችን አትሞ ማሰራጨቱን ያስታወቀው የኢትዮጵያ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት፣ ለፓስፖርት ፈላጊዎች በሁለት ወራት ውስጥ ምላሽ እንደሚሰጥ ገለጸ።

ይህን የተቋሙን የመንፈቅ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ተከትሎም፣ አሁን ላይ ውዝፍ የፓስፖርት ጥያቄ አለመኖሩን፣ የአገልግሎቱ ዋና ዲሬክተር ሰላማዊት ዳዊት፣ ዛሬ ረቡዕ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ተናግረዋል።

ከውጭ ሀገራት ዜጎች ቁጥጥር ጋራ በተያያዘም፣ በኢትዮጵያ በሐሰተኛ ሰነድ ሲኖሩ በነበሩ የውጭ ዜጎች ላይ፣ ከሀገር ማባረርን ጨምሮ የተለያዩ ርምጃዎች እንደተወሰደባቸው ዋና ዲሬክተሯ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG