በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጤፍ ዋጋ በ11 ወራት ከሁለት ዕጥፍ በላይ መጨመሩ ተጠቆመ


የጤፍ ዋጋ በ11 ወራት ከሁለት ዕጥፍ በላይ መጨመሩ ተጠቆመ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:17 0:00

በግጭቶች ሳቢያ የገበያ ተደራሽነታቸው እንደተስተጓጎለ የተገለጸው የጤፍ፣ የሽንኩርት እና መሰል መሠረታዊ ፍጆታዎች ዋጋ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየናረ መምጣቱን ሸማቾች ገልጸዋል።

የአሜሪካ ድምፅ ዛሬ ረቡዕ ያነጋገራቸው ሸማቾች እንዳመለከቱት፣ በተለይ የጤፍ ዋጋ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ፣ ከሁለት ዕጥፍ በላይ ጨምሯል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት በምኅጻሩ ዩኤን-ኦቻ፣ ትላንት ይፋ ባደረገው መረጃ፣ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በቀጠሉት ግጭቶች ምክንያት፣ የጤፍ ዋጋ እስካለፈው ታኅሣሥ ባሉት 11 ወራት ውስጥ፣ በ105 በመቶ ጨምሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG