በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ከፊል የኤምባሲ ሠራተኞቿን ከሄይቲ አስወጣች


ፎቶ ሮይተርስ (መጋቢት 7፣ 2024)
ፎቶ ሮይተርስ (መጋቢት 7፣ 2024)

በሄይቲ የአሜሪካ ኤምባሲ እጅግ አስፈላጊ ያልሆኑ ሠራተኞችን በአየር ማንሳቱን የአሜሪካ ጦር ዛሬ አስታውቋል። ኤምባሲውን የሚጠብቁ ተጨማሪ ወታደሮችን መመደቡንም ጦሩ ጨምሮ አስታውቋል።

የሄይቲ መዲና ፖርት ኦ ፕሪንስ በአብዛኛው በተቀናቃኝ የወሮ በሎች ቡድን ቁጥጥር ሥር ስትሆን፣ ግጭቱ በማየሉ ባለፈው እሁድ የአስችኳይ ግዜ አዋጅ ታውጇል። ይህም የሆነው የአገሪቱ ጠቅላይ ምኒስትር አሪየል ሄንሪ ናይሮቢ ውስጥ በሚገኙበት እና በተመድ አስተባባሪነት እና በኬንያ ፖሊሶች መሪነት ወደ ሄይቲ ዓለም አቀፍ የፀጥታ አስከባሪ ቡድን በፍጥነት በሚላክበት መንገድ ላይ በመነጋገር ላይ ሳሉ ነው። በሺሕ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መዲናይቱን ለቀው ወጥተዋል።

የአሜሪካ ጦር የደቡብ ዕዝ እንዳስታወቀው፣ ከሄይቲ የኤምባሲ ሠራተኞችን የማስወጣቱ ሥራ፣ በየትኛውም ዓለም በአሜሪካ ኤምባሲዎች ላይ የሚደረግ የደህንነት ጥበቃ አካል መሆኑን እና አንድም የሄይቲ ዜጋ በወታደራዊ አውሮፕላኑ ተይዞ እንዳወልጣ አስታውቋል።

በኬንያ የፖሊስ ኃይል መሪነት ዓለም አቀፍ የፀጥታ አስከባሪ ቡድን የመላኩ ጉዳይ፣ በናይሮቢ ሕጋዊ ጥያቄዎች በመንሳታቸው እና በመንግስት ላይ ክሶች በመመሥረታቸው በተፈለገበት ፍጥነት ሊካሄድ አልቻለም።

ትናንት ቅዳሜ የአሜሪካው የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ከኬንያው ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ ጋራ መነጋገራቸው ሲታወቅ፣ ከአገራት የተውጣጣ የፀጥታ አስከባሪ ልዑክ ወደ ሄይቲ በመላክ ጉዳይ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት አስታውቀዋልን ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG