በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሴኔጋል የምርጫ ዘመቻ ተጀመረ


በሴኔጋል ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች አንዱ (ፎቶ ኤኤፍፒ፤ የካቲት 24፣ 2024)
በሴኔጋል ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች አንዱ (ፎቶ ኤኤፍፒ፤ የካቲት 24፣ 2024)

በሴኔጋል ከሁለት ሳምንት በኋላ፣ መጋቢት 15 ቀን ሊካሄድ ለታቀደው ምርጫ ተወዳዳሪዎች የምረጡኝ ዘመቻቸውን ትናንት ጀምረዋል። በሴኔጋል ምርጫው እንዲዘገይ መወሰኑን ተከትሉ አገሪቱ ለሳምንታት ቀውስ ውስጥ የሰነበተች ሲሆን፣ በተደረገው ዓለም አቀፍ እና የአገር ውስጥ ጫና የማኪ ሳል መንግስት ምርጫውን በአጭር ግዜ ውስጥ እንዲያደርግ ተገዷል።

ካሊፋ ሳል የተባሉ የመዲናይቱ ዳካር የቀድሞ ከንቲባ በተለያዩ የከተማይቱ ክፍሎች በመዘዋወር ደጋፊዎቻቸውን ሲያነቃቁ ውለዋል።

“ከወራት ቀውስ በኋላ የምርጫ ዘመቻ በመጀመራችን ደስተኛ ነኝ” ሲሉ ተደምጠዋል።

ካሊፋ ሳል ከማኪ ሳል ጋር ስማቸው ቢመሳሰልም፣ ዝምድና እንደሌላቸው ታውቋል። በመቶ የሚቆጠሩ ደጋፊዎቻቸው በዘፈን እና በፈንጠዝያ ተቀብለዋቸዋል።

ካሊፋ ሳል ለውድድር ከቀረቡት 19 እጩዎች መካከል የወቅቱን ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ይተካሉ ተብለው የሚጠበቁ ናቸው።

የሴኔጋል ምርጫ ከሁለት ሳምንት በፊት ሊካሄድ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረ ሲሆን፣ የማኪ ሳል መንግስት በወራት እንዲራዘም ለማድረግ ሲያቅድ፣ የአገሪቱ ሕገ መንግስታዊ ም/ቤት የመንግስትን ሃሳብ በመሻር ምርጫው መጋቢት 15 ቀን እንዲደረግ ወስኗል።

የማኪ ሳል መንግስት ምርጫውን ለማራዘም ያደረገው ሙከራ በመፈቅለ መንግስት በሚተራመሰው ምዕራብ አፍሪካ የመረጋጋት ተምሳሌት የነበረችውን አገር ቀውስ ውስጥ ከቷት ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG