በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል ከ20ሺሕ በላይ ተማሪዎች በረኀብ ምክንያት ትምህርት አቋረጡ


በትግራይ ክልል ከ20ሺሕ በላይ ተማሪዎች በረኀብ ምክንያት ትምህርት አቋረጡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:30 0:00

በትግራይ ክልል በ57 ወረዳዎች በረኀብ ምክንያት 20ሺሕ ተማሪዎች ትምህርት ማቋረጣቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡ ይህ የተማሪዎቹ አኃዝ፣ በተገባደደው የካቲት ወር ብቻ የተመዘገበ እንደሆነ ቢሮው ገልጿል፡፡

በቂ የርዳታ ምግብ በአፋጣኝ ካልደረሰና በትምህርት ቤቶች የምገባ መርሐ ግብር ካልተጀመረ፣ ለመዘጋት የተቃረቡ ትምህርት ቤቶች ብዙዎች እንደኾኑ፣ የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ረዳኢ ገብረ እግዚአብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የሕፃናት አድን ድርጅት በኢትዮጵያ፣ በክልሉ በመጠለያ ማዕከላት ከሚገኙ ሚሊዮን ሰዎች 20 በመቶ የሚኾኑት ሕፃናት ለምግብ እጥረት እንደተጋለጡ አመልክቷል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG