ተቋሙ በተጨማሪም፣ ልዩ ልዩ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያርፉባቸውን ቤቶች በማዘጋጀት የጤና፣ የፍትሕ እና የሥነ ልቡና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ የተሰናዳው ዘገባ ይቀጥላል፡፡
ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን፣ የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. “አካታችነትን ማነቃቃት” በሚል መሪ ቃል ታስቦ ውሏል፡፡ ዕለቱን በማሰብ፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል፣ ሴቶች በወሊድ እና በወር አበባ ወቅት ወደ ጫካ እንዲገቡና እንዲገለሉ የሚገደዱበት አጉል ልማድ ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር፣ ከሁለት ዐሥርት ዓመታት በላይ የሠራን ተቋም ጋብዟል፡፡ ተቋሙ “ምዥዥጓ ሎካ” ይባላል፡፡ አሁን በሕይወት በሌለችው ወጣት ትርሃስ መዝገበ አማካይነት የተመሠረተ ተቋም ነው፡፡
ተቋሙ በተጨማሪም፣ ልዩ ልዩ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚያርፉባቸውን ቤቶች በማዘጋጀት የጤና፣ የፍትሕ እና የሥነ ልቡና ድጋፍ እንዲያገኙ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ ጉዳይ ላይ የተሰናዳው ዘገባ ይቀጥላል፡፡