በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዋስትና የተፈቀደላቸው አቶ በቴ ኡርጌሳ አልተፈቱም


ዋስትና የተፈቀደላቸው አቶ በቴ ኡርጌሳ አልተፈቱም
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:27 0:00

ትላንት ረቡዕ፣ በአዲስ አበባ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለሦስተኛ ጊዜ የቀረቡት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ በ100 ሺሕ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ቢወሰንላቸውም አለመፈታታቸውን፣ ጠበቃቸው አቶ ቦና ያዘው ገለጹ።

ቤተሰቦቻቸው የዋስትና ገንዘቡን፣ ዛሬ ኀሙስ ከፍለው የመልቀቂያ ትዕዛዝ ለፖሊስ መምሪያው ማስገባታቸውን አመልክተዋል። ሆኖም ፖሊስ፣ ነገ ይግባኝ እንደሚጠይቅባቸውና ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው በመግለጽ እንደማይለቃቸው በማስታወቁ ሳይፈቱ መቅረታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ፣ የካቲት 14 ቀን 2016 ዓ.ም. ከፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ ጋራ ቃለ ምልልስ እያደረጉ ባሉበት ወቅት ነበር በቁጥጥር ሥር የዋሉት፡፡

መጀመሪያ ላይ፣ “የሀገርን ምስጢር አሳልፎ በመስጠት” መጠርጠራቸው እንደተገለጸላቸው የተናገሩት ጠበቃቸው አቶ ቦና፣ በኋላ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ደግሞ፣ “ሸኔ እና ፋኖ አዲስ አበባ ላይ ሁከት እንዴት ማሥነሳት እንደሚችሉ ስትራቴጂ አውጥተዋል፤” የሚል ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር ጠበቃቸው ተናግረዋል፡፡

ለሦስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት በቀረቡበት ወቅትም፣ ፖሊስ ተጨማሪ 14 የምርመራ ቀናትን ቢጠይቅባቸውም ፍርድ ቤቱ ግን፣ ከዚህ በፊት የምርመራ ሒደቶች መጓተታቸውንና አሁንም ፖሊስ ማቅረብ ያለበትን ማስረጃ አላቀረበም፤ በሚል የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው መወሰኑን አስረድተዋል፡፡

ከአቶ በቴ ጋራ በቁጥጥር ሥር ውሎ የነበረው ፈረንሳዊው ጋዜጠኛ አንቷን ጋሊንዶ፣ የዛሬ ሳምንት ከእስር ተለቅቆ ወደ ሀገሩ መመለሱ ይታወሳል፡፡

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG