የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን እየተጠቀሙ “የባህል ሕክምና እንሰጣለን” በሚል የሚያጭበረብሩ ግለሰቦች እየተበራከቱ እንደመጡ፣ የኢትዮጵያ ባህላዊ መድኃኒት ሕክምና አዋቂዎች ማኅበር አስታወቀ፡፡
የጤና ሚኒስቴር ደግሞ፣ በዘመናዊ ሕክምና የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ከቅጠላቅጠሎች ጋራ ቀላቅለው በመስጠት የኅብረተሰቡን ጤና ለአደጋ ያጋለጡ ስለመኖራቸው ገልጿል፤ ኅብረተሰቡም ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ አሳስቧል፡፡
የአሜሪካ ድምፅ ያናገራቸው የሕግ ባለሞያ አቶ ያሬድ ሥዩም፣ የኅብረተሰቡን ጤና አደጋ ላይ የሚጥሉ ማጭበርበሮች በወንጀል ሕጉ እንደሚያስጠይቁ ተናግረዋል፡፡ ይኹንና የፍትሕ ሚኒስቴር፣ እስከ አሁን ጉዳዩን የተመለከቱ ክሶች ከኅብረተሰቡ እንዳልደረሱት ጠቅሷል፤ ማንኛውም ተበዳይ ካለ ግን ለፍትሕ ተቋማት ማመልከት እንደሚችል ሚኒስቴሩ ጠቁሟል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።