ኢትዮጵያ፣ በእንጦጦ የኦብዘርቫቶሪ እና ምርምር ማዕከል ውስጥ የሚገኘው የብዝኀ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያዋ፣ ለሌሎች ተቋማት እና ሀገራት የመረጃ አገልግሎት መስጠት እንደጀመረ አስታወቀች፡፡
የሳተላይት ግንኙነት፣ መረጃን መቀበል፣ መረጃን መተንተንና መረጃን መስጠት፣ ጣቢያው ከጀመራቸው አገልግሎቶች እንደሚጠቀሱ፣ በኢትዮጵያ የስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የሳተላይት ኦፕሬሽን መሪ ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር መልአኩ ሙካ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ አስረድተዋል፡፡በዚህም ገቢ እንደሚያስገኝ ተናግረዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡት የስፔስ ሳይንስ እና የአስትሮኖሚ ተመራማሪው ዶር. ሰሎሞን በላይ ደግሞ፣ በኢትዮጵያ ይፋ የተደረገው አገልግሎት፣ ከሌሎች ሀገራትም ጠቃሚ መረጃ ለማግኘት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል፡፡ ኾኖም፣ መንግሥት ይህን አገልግሎት ለግሉ ዘርፍ በመተው፣ በዐቅም ግንባታ እና በመሠረተ ልማት ማስፋፋት ሥራዎች ላይ ቢያተኩር እንደሚሻል አስገንዝበዋል፡፡
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።