በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በግዳ አያና ወረዳ በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ


በግዳ አያና ወረዳ በታጣቂዎች ተፈጸመ በተባለ ጥቃት ሦስት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:25 0:00

በምሥራቅ ወለጋ ዞን የግዳ አያና ወረዳ ባለፈው ሣምንት ረቡዕ የካቲት 13/2016 ዓ.ም በሕዝብ ማጓጓዣ ተሽከርካሪ ላይ በታጣቂዎች እንደተፈጸመ በተገለጸ ጥቃት፣ ሦስት ሰዎች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት ሰዎች መቁሰላቸውን፣ ነዋሪዎች እና የወረዳው ባለሥልጣናት ተናገሩ።

ጥቃቱ፣ “ጽንፈኛ ፋኖ” ሲሉ በጠሯቸው ታጣቂዎች መፈጸሙንም፣ ነዋሪዎቹ እና ባለሥልጣናቱ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ከነቀምቴ ከተማ ወደ ግዳ አያና እና ወደ ጉትን ወረዳዎች በሚወስዱ መንገዶች ላይ፣ የግድያ እና አፈና ድርጊቶች እንደቀጠሉም አመልክተዋል፡፡

የግዳ አያና ሆስፒታል ኃላፊ ዶክተር መልካሙ አዱኛም፣ በጥቃቱ ሕይወታቸው ያለፈ የሦስት ሰዎች አስከሬን ወደ ሆስፒታሉ መምጣቱንና ሌሎች የቆሰሉ ሁለት ሰዎችም ሕክምና እንዳገኙ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

የግዳ አያና ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አመኑ ዲንሳ፣ በግዳ አያና ወረዳ ደጋ ጅጊ በተባለ ስፍራ እንደተፈጸመ በገለጹት በዚሁ ጥቃት፣ ሦስት ሰዎች መገደላቸውን አረጋግጠዋል፡፡ ከግድያውም ጋራ በተገናኘ አራት ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው ነው፤ ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG