በዚህ ውድድር የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን ሰብራ አሜሪካዊቷ ኤሌ ፔዬሬ የወርቅ፣ ኬኒያዊቷ አትሪስ ቼፕኮኤች ደግሞ የነሃስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።ኢትዮጵያውያኑ ለምለም ሃይሉ እና ሂሩት መሸሻ ስድስተኛ እና ሰባተኛ ደረጃን ይዘው ጨርሰዋል። በወንዶቹ የ3ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ የነሃስ ሜዳሊያ አስገኝቷል። የታላቋ ብሪታኒያው አትሌት ጆሽ ኬር የወርቅ ሜዳሊያውን ሲወስድ፣ አሜሪካዊው ያሬድ ንጉሴ ደግም የብር ሜዳሊያ አስገኝቷኣል። በቡድን ሥራ ትልቁን ድርሻ የወሰደው አትሌት ጌትነት ዋለ አራተኛ በመውጣት የዲፕሎማ አግኝቷል:: ኤቢሳ ነገሰ ከስፍራው ያጠናቀረውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጁላይ 27, 2024
በማላዊ ለአሳዳጊ አልባ ሕፃናት መጠጊያ የኾነው ማዕከል
-
ጁላይ 27, 2024
በጠፈር ምርምር ትምህርት መርሐ ግብር የተመረቁ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
-
ጁላይ 26, 2024
የኢትዮጵያውያኑ ባህላዊ ማዕድ እና አብሮነት ታዛ - በሚልዋኪ
-
ጁላይ 26, 2024
የፕሬዝደንት ጆ ባይደን ንግግር
-
ጁላይ 23, 2024
አምስት ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በኮዲንግ ሞያ የማብቃት መርሐ ግብር ይፋ ኾነ