በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ የሰላም አስከባሪዎቹን ከ25 ዓመታት በኋላ ከኮንጎ ማስወጣት ጀመረ


ተመድ የሰላም አስከባሪዎቹን ከ25 ዓመታት በኋላ ከኮንጎ ማስወጣት ጀመረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:57 0:00

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪዎቹን ከ25 ዓመታት በኋላ በሁከት ከሚታመሰው የኮንጎ ዲሞክራሲያዊት ሪፐብሊክ ምሥራቃዊ አካባቢ ማስወጣት ጀምሯል፡፡

ሞንስኮ (MONUSCO) በመባል የሚታወቀው የተባበሩት መንግሥታት የሰላም አስከባሪ በሀገሪቱ ምስራቅ የሚገኘውን የካማንዮላ ጦር ሰፈር ትናንት ረቡዕ እኤአ የካቲት 28 ለኮንጎ ባለሥልጣናት አስረክቧል፡፡

በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2005 የተመሰረተው የካማንዮላ ጦር ሰፈር ሲቪሎችን የመጠበቅ እና በምስራቅ ደቡብ ኪቩ ግዛት ጸጥታን የማስጠበቅ ኃላፊነት ተሰጥቶት ነበር።

በርክክብ ሥነ-ሥርዓት ላይ የሞኑስኮ ዋና ኃላፊ ቢንቱ ኬታ፣ ዝውውሩ ለተልዕኮው ማብቃት ማሳያ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

እንደ ሞንስኮ ገለጻ፣ ዝውውሩ ከደቡብ ኪቩ ለመልቀቅ ከመጀመሪያዎቹ የተነሳሽነት ርምጃዎች አንዱን ያመለክታል።

ኬታ ከኮንጎ ባለሥልጣናት ጋራ ርክክቡን በስርዓት እና በኃላፊነት ለመወጣት በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ሞንስኩ ወደ 15,000 የሚጠጉ የሰላም አስከባሪ ኃይሎች ያሉት ሲሆን በደቡብ ኪቩ፣ ሰሜን ኪቩ እና ኢቱሪ በተጨናነቁ ግዛቶች ይሠራል።

ዘገባው የሮይተርስ ነው ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG