በጋዛው ጦርነት የረመዳን ጾም ከመግባቱ አስቀድሞ ጊዜያዊ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ አደራዳሪዎች ብርቱ ግፊት እያደረጉ ይገኛሉ።
ሆኖም፣ 30ሺሕ የሚደርሱ ፍልስጥኤማውያን በተገደሉበት የእስራኤል የጋዛ ወታደራዊ ዘመቻ፣ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን በሰጡት ድጋፍ ሳቢያ ከወደ ሚሽጋን የቁጣ መልእክት እየተሰማ ነው።
የመጪው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የቅድሚያ ውጤቶች እንደሚያሳዩት፣ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው አረብ አሜሪካውያን በሚኖሩባት የሚሽጋን ግዛት፣ በርካታ መራጮች በምርጫ ካርዳቸው ላይ “ድምፅ ያልሰጠ” የሚለውን ምልክት በማቅለም ለፕሬዚዳንት ባይደን ድምፃቸውን መንፈጋቸውን እያሳዩ ይገኛሉ።
ይህቺው የሚሽጋን ግዛት፣ አንድ ጊዜ የዴሞክራቱን እጩ ሌላ ጊዜ ደግሞ የሪፐብሊካንን እጩ በመምረጥ በፕሬዝዳንታዊው የምርጫ ሒደት ወሳኝ ተደርጋ ትታያለች፡፡
የአሜሪካ ድምፅዋ የዋይት ሐውስ ቢሮ ኃላፊ ፓትሲ ዊዳኩስዋራ፣ ሌላዋ ዘጋቢያችን ዶራ መኩዋር ከሚሽጋን ያጠናቀረችውን አጣምራ ያደረሰችንን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ማርች 14, 2025
በአፍሪካ የኅይል አቅርቦት ላይ ያተኮረውና በዋሽንግተን ዲሲ የተካሔደው ጉባኤ
-
ማርች 14, 2025
የኢትዮጵያውያት ሴቶች ጥያቄ ምንድን ነው? - የአድማጭ ተመልካቾች አስተያየት
-
ማርች 13, 2025
አርቲስት አንዱዓለም ጎሣ ተጨማሪ 13 ቀናትን በእስር እንዲቆይ ፍርድ ቤት ፈቀደ
-
ማርች 13, 2025
ሩሲያ የተቆጣጠረቻቸውን የዩክሬን ግዛቶች እንደያዘች መቀጠል ትሻለች