በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ ቀያቸው የተመለሱ የግጭት ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ


ወደ ቀያቸው የተመለሱ የግጭት ተፈናቃዮች ችግር ላይ መሆናቸውን ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:37 0:00

ባለፉት ሁለት ዓመታት ከምሥራቅ ወለጋ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በነበሩ ግጭቶች ከተፈናቀሉ 350ሺሕ ተፈናቃዮች መካከል ከ220ሺሕ በላይ የሚሆኑት ወደቀዬአቸው እንደተመለሱ፣ የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት(ቡሳ ጎኖፋ) አስታወቀ።
ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ ተመላሾች፣ ወደ ቀድሞ ኑሯቸው ለመመለስ በሚያደርጉት ጥረት በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል።
ከእነዚኽ ተፈናቃዮች ውስጥ በአማራ ክልል ደብረ ብርሃን ከተማ ተጠልለው የነበሩና ሰሞኑን ወደ ቀዬአቸው የተመለሱ 680ሰዎች፣ አሁንም የጸጥታ ችግር እንዳለባቸው አመልክተዋል። በዞኑ ወደምትገኘው ጎቡ ሰዮ ወረዳ ከተመለሱም በኋላ ወደ ቀበሌዎቻቸው መሔድ አለመቻላቸውንና እስከ አሁን የሚገኙትም በወረዳው ዋና ከተማ አኖ እንደኾነም ገልጸዋል።
የቅሬታውን ተገቢነት የጠቀሱት የምሥራቅ ወለጋ ዞን የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ለቺሳ፣ ለጊዜው ተመላሾቹ የተሻለ የጸጥታ ኹኔታ ባለበት ስፍራ በጥበቃ እየኖሩ እንደሚገኙ ገልጸዋል፤ “የጸጥታው ችግር በአስተማማኝ መልኩ ሲቀረፍም ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ ይደረጋል፤” ብለዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG