በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በናዳ የተቀበሩ የደላንታ ኦፓል አምራች ቤተሰቦች ዕርማቸውን እያወጡ ነው


በናዳ የተቀበሩ የደላንታ ኦፓል አምራች ቤተሰቦች ዕርማቸውን እያወጡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:27 0:00

በደላንታ ወረዳ የዋሻ ውስጥ ባህላዊ የኦፓል ማምረት ሥራ ላይ ሳሉ በናዳ የተዋጡ ወጣቶችን በሕይወት የማግኘቱ ተስፋ የተመናመነባቸው የቤተሰብ አባላት፣ ኀዘን እየተቀመጡና ዕርማቸውን እያወጡ እንደሚገኙ ተናገሩ፡፡

በናዳ የተቀበሩት አምራቾች ዛሬ ማክሰኞ 19ኛ ቀናቸውን የያዙ ሲሆን፣ “ከዚህ በኋላ በሕይወት የመገኘታቸው ዕድል የመነመነ ነው፤” ሲሉ፣ ቤተሰቦቻቸው ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል። “አስከሬናቸውን አግኝተን ቀብራቸውን በክብር አለመፈጸማችን ኀዘናችንን አባብሶታል፤” ብለዋል።

እስከ አሁን ባለው መረጃ፣ ዋሻው ውስጥ ገብተው የደረሱበት ያልታወቁት አምራቾች ቁጥር፣ ከስምንት ያላነሰ እንደኾነ ኀዘንተኞቹ አመልክተዋል። የደላንታ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፣ ላለፉት 19 ቀናት ዋሻው የተናደባቸውን አምራቾች በባህላዊ እና በዘመናዊ መንገድ ለመታደግ የተደረጉ ጥረቶች ውጤት አለማስገኘታቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG