የሩስያን ወታደራዊ ግስጋሴ ለመግታት፣ ለዩክሬን የሚያስፈልጉ የጦር መሣሪያዎችን በፍጥነት ማቅረብ እንደሚያፈልግ፣ አውሮፓ እና ዩናይትድ ስቴትስ፣ ትላንት እሑድ ተመሳሳይ አጽንዖት በመስጠት አሳስበዋል።
በትይዩም፣ በንጹሐን ላይ እየደረሰ ያለው ሥቃይ እንዲቆምና ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ትኩረት እንዲሰጣቸው ተጠይቋል።
ቬሮኒካ ባልደራስ ኢግሌሲያስ ያደረሰችን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።