በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ህወሓት ሁለት አመራሮቹን ከአመራርነት እና ከአባልነት አሰናበተ


ህወሓት ሁለት አመራሮቹን ከአመራርነት እና ከአባልነት አሰናበተ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:36 0:00

ህወሓት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል የነበሩትን ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂምንና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባል የነበሩትን ወይዘሮ ሙሉ ገብረ እግዚአብሔርን ከፓርቲው አመራርነት እና ከአባልነት ማሰናበቱን አስታወቀ። ፓርቲው ሁለቱን አመራሮች ያሰናበተው ለፌደራል መንግሥት ምስጢር አሳልፈው ሰጥተዋል በሚል እንደኾነ አስታውቋል።

ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም “አሁን እውነት የሚነገርበት ጊዜ አይደለም፤ ሐቁ ወደፊት ይወጣል፤” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸው ሰጥተዋል።

የህወሓት ጽሕፈት ቤት የፕሮፓጋንዳ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ኢያሱ ተስፋዬ በበኩላቸው፣ ሁለቱም አመራሮች እንዲሰናበቱ የተደረጉት፣ በጦርነቱ ወቅት በነበራቸው አሰላለፍ ላይ ተመሥርቶ በተካሔደ ግምገማ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።

ከትላንት ኀሙስ ጀምሮ የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባውን እያካሔደ ያለው ህወሓት፣ በጦርነቱ ወቅት በፌደራሉ መንግሥት በቁጥጥር ሥር ውለው የነበሩ ሌሎች ስድስት የሥራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ አባላት ደግሞ ወደነበሩበት የፓርቲ ኃላፊነት እንዲመለሱ ወስኗል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG