በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዩናይትድ ስቴትስ 15 ሚሊዮን ዶላር ትመድባለች


የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዩናይትድ ስቴትስ 15 ሚሊዮን ዶላር ትመድባለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:19 0:00

የትግራይ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋም ዩናይትድ ስቴትስ 15 ሚሊዮን ዶላር እንደምትመድብ ማይክ ሐመር አስታወቁ። የዩናይትድ ስቴትስ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ይህን ያስታወቁት ትላንት ረቡዕ በበይነ መረብ በሰጡት መግለጫ ነው። ሐመር በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋራ መቀሌ ላይ ውይይት አካሂደዋል።

ውይይቱ ከፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጋራ የተያያዘ እንደኾነ፣ በውይይቱ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች ገልጸዋል፡፡ አምባሰደር ማይክ ሐመር፣ የኤርትራ ኀይሎች በኢትዮጵያ ግዛት እስከ አሁን መቆየታቸውና ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው አለመመለሳቸው እንደሚያሳስባቸው፣ በዚያው በመቀሌ እንዳሉ በሰጡት የበይነ መረብ መግለጫ ተናግረዋል፡፡

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG