በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዝብ ብዙኀን መገናኛዎች “የገዥው ፓርቲ መሣሪያ ኾነዋል” ተባለ


የሕዝብ ብዙኀን መገናኛዎች “የገዥው ፓርቲ መሣሪያ ኾነዋል” ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:55 0:00

በኢትዮጵያ ያሉ የሕዝብ ብዙኀን መገናኛዎች፣ ሕዝባዊ ኃላፊነታቸውን እየተወጡ እንዳልኾነ፣ አንድ ጥናት አመለከተ። “መልካም አስተዳደር በአፍሪካ” በተሰኘ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት የተደገፈው ይኸው ጥናት፣ በሕዝብ ሀብት የሚተዳደሩት የአገሪቱ የሕዝብ ብዙኀን መገናኛዎች፣ የኤዲቶሪያል ነጻነት እንደሌላቸውም ያሳያል፡፡

ጥናቱን ያካሔዱት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና ኮምዩኒኬሽንስ መምህር ዶክተር ጌታቸው ድንቁ፣ የሕዝብ ብዙኀን መገናኛ ተቋማቱ ሕዝባዊ ኃላፊነታቸውን መወጣት ሲገባቸው፣ ለገዥው ፓርቲ ያደሉ ዘገባዎችን በመሥራት ላይ ተጠምደዋል፤ ይላሉ፡፡

ይኸው አካሔድ ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የገለጹት ዶር. ጌታቸው፣ አሠራራቸው በዚኹ ሊቀጥል አይገባም፤ ብለዋል፡፡ በጉዳዩ ላይ አስተያየት የሰጡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎችም፣ የብዙኀን መገናኛ ተቋማቱ፣ ተገቢ አገልግሎት እንደማይሰጧቸው ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።

XS
SM
MD
LG