በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለተፈናቃይ የዴቻ ወረዳ አርሶ አደሮች ይዞታቸው እንዲመለስላቸው ኢሰመኮ አሳሰበ


ለተፈናቃይ የዴቻ ወረዳ አርሶ አደሮች ይዞታቸው እንዲመለስላቸው ኢሰመኮ አሳሰበ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00

ለተፈናቃይ የዴቻ ወረዳ አርሶ አደሮች ይዞታቸው እንዲመለስላቸው ኢሰመኮ አሳሰበ

ከደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ የተፈናቀሉ 267 አርሶ አደሮች እና ቤተሰቦቻቸው፣ በአሳሳቢ ችግር ውስጥ እንደሚገኙ ኢሰማኮ አስታወቀ።

አርሶ አደሮቹ መሬታቸው እንደተነጠቀባቸው ለአሜሪካ ድምፅ የገለጹት የኮሚሽኑ ምክትል ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ፣ በአስቸኳይ ይዞታቸው ተመልሶላቸው በቀዬአቸው እንዲቋቋሙ ይደረግ ዘንድ አሳስበዋል።

በካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ፣ ከ2011 ዓ.ም. አንሥቶ ደረሰብን በሚሉት ማንነት ተኮር ጥቃት የተፈናቀሉ አርሶ አደሮች፣ ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን በስልክ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የክልሉ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ግን፣ “የተፈናቀሉ ሰዎች ስለመኖራቸው አላውቅም፤ የሰማኹትም ነገር የለም፤” ብሏል፡፡ የሐዋሳው ዘጋቢያችን ዮናታን ዘብዴዎስ ተጨማሪ ዘገባ ልኳል። ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG