በትግራይ ክልል፣ የድኅረ ጦርነት መልሶ ግንባታ ሥራው መፋጠን አለበት፤ ሲል የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አሳሰበ።
ኮሚሽኑ በክልሉ፣ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ክትትል ማካሔዱን ገልጾ ዛሬ ማክሰኞ ባወጣው ሪፖርት፣ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው የመመለስ ሥራው “በጣም ውሱንና ያልቀጠለ ነው፤” ብሎታል።
በትግራይ ክልል በጦርነቱ የተጎዱ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት ወደ ሥራ እየገቡ ቢኾንም፣ አሁንም ከፍተኛ ድጋፍ እና ትብብር እንደሚያስፈልጋቸው ኮሚሽኑ አመልክቷል፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያዳምጡ።