ግብፅ ጋዛን በሚያዋስነው በሲናይ ባህረ ገብ መሬት ላይ ትልቅ የጥበቃ ኬላ የሚመስል ነገር እየገነባች መሆኑ ተነገረ፡፡
ግንባታው ከጋዛ ሰርጥ ጎርፈው የሚወጡ ፍልስጤማውያን ፍልስተኞችን ለመቀበል እየተዘጋጀች ይሆናል የሚል ጥርጥሬ ፈጥሯል፡፡
የሳተላይት ምስሎች ከ5 እስከ 20 ካሬ ኪ.ሜ. በተደለደለ ስፍራ ላይ ከፍ ባለ የኮንክሪት ግድግዳ እየተገነባ የሚታይ ስፍራ መኖሩን ያመላከቱ መሆኑ ተዘግቧል፡፡
የአገር ውስጥ የግንባታ ሥራ ተቋራጮችን ጠቅሶ ሲናይ ፋውንዴሽን የተባለው የሰአብአዊ መብት ተሟጋቾች ቡድን እንደዘገበው፣ ግንባታው 7ሜትር ከፍታ ያለው ግንብን ያካተተ መሆኑን፣ ከሳተላይት ምስሎች ጋር ተያይዞ የወጣው ዘገባ አመልክቷል፡፡
ስለ ዘገባዎቹ የግብጽ መንግሥት በይፋ የሰጠው አስተያየት የለም፡፡
የጋዛው ጦርነት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን የጋዛ ህዝብ ከሰሜን ጋዛ ወደ ደቡብ እንዲጋዝና በግብፅ ድንበር አቅራቢያ በምትገኘው ራፋህ ከለላ እንዲሻ ያስገደደው መሆኑ ተዘግቧል፡፡
መድረክ / ፎረም