አንድ የምክር ቤት አባል በአሜሪካ ብሔራዊ ደኅንነት ላይ የተጋረጠ አደጋ መኖሩን ማስጠንቀቃቸውን ተከትሎ፣ ሩሲያ ፀረ ሳተላይት መሣሪያን በማበልጸግ ላይ እንደኾነች ማረጋገጡን፣ ዋይት ሐውስ ትላንት አስታውቋል።
ድርጊቱ፣ ሩሲያን፥ የህዋ ላይ የጅምላ ጨራሽ መሣሪያ ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚከለክለውን ስምምነት በመጣስ ሊያስጠይቃት እንደሚችል የዋይት ሐውስ ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው። ጉዳዩ በአሁኑ ወቅት፣ የደኅንነት ስጋት አለመኾኑን የገለጹት ባለሥልጣናቱ፣ አሜሪካውያን መረበሽ እንደሌለባቸውም መልዕክት አስተላልፈዋል። የምክር ቤት አባላት ደግሞ፣ በጉዳዩ ላይ በር ዘግተው እየመከሩ ነው።
የቪኦኤዋ አኒታ ፓወል የላከችውን ዘገባ ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።