በዌስት ባንክ የሚኖሩ ፍልስጥኤማውያን፣ ከመስከረም 26ቱ የሐማስ ጥቃት ወዲህ፣ በእስራኤላውያን ሰፋሪዎች የሚፈጽሙባቸው ጥቃቶች በከፍተኛ መጠን እንደጨመሩ ተናግረዋል።
ጥቃቶቹ ያየሉት፣ ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ለማድረግ ታልመው እንደሆነም አስረድተዋል፡፡
ይኹንና ውንጀላዎቹን ያስተባበለው የሰፈራ ጉዳዮች ምክር ቤት፣ ጥቃት የሚፈጸምባቸው ኹኔታዎች ቀንሰዋል፤ ይላል።
ሊንዳ ግራድስቲን ከዌስት ባንክ የደቡባዊ ሄብሮን ሂልስ ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ አሉላ ከበደ ወደ አማርኛ መልሶታል።