ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ፣ ከ12 ሺሕ በላይ ተፈናቃዮች በኤርትራ ኀይሎች ከተያዙት ቦታዎች እና የፌደራል መንግሥቱ "አከራካሪ" ሲል ከሚገልጻቸው የትግራይ እና የአማራ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች እንደተፈናቀሉ፣ የትግራይ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።
የኮሚሽኑ ኃላፊ ዶክተር ገብረ ሕይወት ገብረ እግዚአብሔር ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በክልሉ የቀድሞ ተፈናቃዮች ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ እየተጠየቀ ባለበት ኹኔታ፣ አዲስ ተፈናቃዮች መጨመራቸው ሰብአዊ ቀውሱን የሚያባብስ ነው፤ ብለዋል።
በክልሉ ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን እንዳባጉና ወረዳ የተፈናቃዮች ማዕከል ውስጥ የሚገኙና በቅርቡ እንደተፈናቀሉ የገለጹ አስተያየት ሰጪዎች፣ ይኖሩበት በነበረው አካባቢ ያለው የጸጥታ ችግር የፈጠረባቸው ስጋት እና የረኀብ አደጋ ለመፈናቀላቸው ምክንያት እንደኾነ ገልጸዋል።
በጉዳዩ ላይ፣ ከአማራ ክልል አመራሮች አስተያየት እና ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም። የክልሉ አመራሮች፣ ከዚህ ቀደም የቀረቡ ተመሳሳይ ውንጀላዎችን ማጣጣላቸው ይታወሳል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።
መድረክ / ፎረም