በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ አፍሪካውያን ቋንቋዎችን ማስተማሯ ዲፕሎማሲያዊ ስልት ወይስ ሌላ?


ሩሲያ አፍሪካውያን ቋንቋዎችን ማስተማሯ ዲፕሎማሲያዊ ስልት ወይስ ሌላ?
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:38 0:00

ሩሲያ የአፍሪካ ሀገራት ቋንቋዎችን በሕዝብ ትምህርት ቤቶቿ ማስተማር ጀምራለች። በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ትምህርት ክፍል መምህሩ ዶክተር ዮናስ አሽኔ፣ ይህን የሩሲያ ውሳኔ “ዲፕሎማሲያዊ ስልት” ነው ይላሉ፡፡ ይኸውም በአፍሪካ እንዲኖራት ለምትፈልገው ቅቡልነት የምትከተለው መንገድ እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡

በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የዲፕሎማሲ እና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ እንዳለ ንጉሤ ደግሞ፣ ሩሲያ እና ቻይና ቋንቋንና ባህልን ጨምሮ የሕዝብ ለሕዝብ ዲፕሎማሲን በመጠቀም በአፍሪካ ተጽእኗቸውን ለማጠናከር ጥረት እንደሚያደጉ ይገልጻሉ።

ኑሯቸውን በሩሲያ ካደረጉ 35 ዓመት ያስቆጠሩት ኢትዮጵያዊው አቶ መድኅን ተፈሪ፣ በሴንት ፒተርስበርግ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የዐማርኛ ቋንቋን ያስተምራሉ፡፡ እርሳቸው እንደሚሉት፣ ሩሲያ ቋንቋዎችን ለዜጎቿ የምታስተምረው “በፈቃደኝነት ላይ ተመሥርታ ነው፡፡”

ዝርዝሩን ከተያያዘው ዘገባ ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG