በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሕዝብ ውሳኔውን ጉዳይ እንደሚያውቁ የአማራ ማንነት ኮሚቴዎች ገለጹ


የሕዝብ ውሳኔውን ጉዳይ እንደሚያውቁ የአማራ ማንነት ኮሚቴዎች ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:53 0:00

በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ ለሚነሣባቸው አከራካሪ ቦታዎች የመጨረሻ ዕልባት ለመስጠት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከመግባባት ላይ መደረሱን እንደሚያውቁ የወልቃይት እና ራያ የአማራ ማንነት ኮሚቴዎች ገልጸዋል።

ለአፈጻጸሙ የሚረዱ እንቅስቃሴዎችም ተጀምረው እንደነበርም የኮሚቴዎቹ አመራሮች ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሰሞኑን ባወጣው መግለጫ የፌዴራሉ መንግሥት “ሕዝበ ውሳኔ እንዲካሔድ ከመግባባት ላይ ተደርሶ ነበር፤” ማለቱ ፍጹም የተሳሳተና በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሠረት በሕገ መንግሥቱ የሚፈቱ ካሏቸው ጉዳዮች ውጭ ነው፤ ብሏል። የፌደራሉ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት፣ ሕዝበ ውሳኔን አስመልክቶ የጠቀሳቸውን ነጥቦች መነሻ ያደረገው መስፍን አራጌ፣ በራያ እና በወልቃይት ዞኖች የሚገኙ የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን አነጋግሯል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG