በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንባ ጠባቂ ተቋም ስለ ትግራይ ድርቅ የጠራ መረጃ እንዲቀርብ ፓርላማ ይዘዘልኝ አለ


እንባ ጠባቂ ተቋም ስለ ትግራይ ድርቅ የጠራ መረጃ እንዲቀርብ ፓርላማ ይዘዘልኝ አለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:43 0:00

የትግራይ ክልል የድርቅ ተረጅዎችን ብዛት አስመልክቶ የጠራ መረጃ እንዲቀርብ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ትዕዛዝ እንዲሰጥ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጠየቀ፡፡

ተቋሙ፣ በሰሜን ኢትዮጵያ ያጋጠመውን የድርቅ ኹኔታ አስመልክቶ፣ ትላንት ማክሰኞ ጥር 21 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ስላደረገው ሪፖርት ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ ዋና እንባ ጠባቂ ዶር. እንዳለ ኃይሌ፣ ከድርቅ ጋራ በተያያዘ ጉዳት በትግራይ ክልል 351 ሰዎች፣ በአማራ ክልል ደግሞ 21 ሰዎች እንደሞቱ ገልፀዋል፡፡

በሪፖርቱ ይዘት ላይ ለአሜሪካ ድምፅ ማብራሪያ የሰጡት፣ የተቋሙ ዋና እንባ ጠባቂ ዶር. እንዳለ ኃይሌ፣ በትግራይ ክልል ሁለት ወረዳዎች እና በዐማራ ክልል ሁለት ወረዳዎች ላይ በተካሔደ ጥናት፣ከድርቅ ጋራ በተያያዘ ጉዳት የሰው ሕይወት ማለፉን አረጋግጠናል፤ ብለዋል፡፡

የትግራይ ክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን በበኩሉ፣ የሟቾቹ ብዛት ከ860 በላይ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ አስታውቋል፡፡የክልል የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽነር ዶር. ገብረ ሕይወት ገብረ እግዚአብሔር ደግሞ፣ በድርቅ ምክንያት ያጋጠመው የሟቾች ቁጥር በተቋሙ ከተጠቀሰውም ከፍ ያለ እንደኾነ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡ ከአማራ ክልል አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ፕሮግራም ማስተባበሪያ ኮሚሽነር ዲያቆን ተስፋው ባያብል አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በጉዳዩ ላይ፣ ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት አስተያየት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡

በቅርቡ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ፣ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ ስላጋጠመው ድርቅ የሰጠው መግለጫ “ፈጽሞ የተሳሳተ ነው፤ ፖለቲካንና ሰብአዊ ድጋፍን ማገናኘት ተገቢነት የለውም፤” በማለት መተቸታቸው ይታወሳል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG