በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ የቤት መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተወሰነ


በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ የቤት መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ ተወሰነ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00

በኢትዮጵያ፣ የአየር ብክለትን ችግር ለመቀነስ፣ መንግሥት ለግል አገልግሎት የሚውሉና በነዳጅ የሚንቀሳቀሱ የቤት መኪኖች ወደ ሀገር እንዳይገቡ መወሰኑን፣ የትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስትሩ ዶር. ዓለሙ ስሜ፣ ትላንት ሰኞ፣ የመሥሪያ ቤታቸውን የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሲያቀርቡ፣ የአየር ብክለትን ለመቀነስ የኤሌክትሪክ መኪኖችን የማበረታታት ሥራ እየተሠራ እንደኾነ ገልጸዋል፡፡ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየት የሰጡ አንድ ባለሞያ ደግሞ፣ ውሳኔው የሸማቹን ሕዝብ ፍላጎት እና ስጋት ከግምት ማስገባት ይኖርበታል፤ ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG