በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች አዋሳኝ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተጠየቀ


በኦሮሚያ እና የደቡብ ክልሎች አዋሳኝ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:30 0:00

የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች፣ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች አዋሳኝ ቀበሌ፣ ከሳምንት በፊት ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ሰላማውያን ሰዎች እንደተገደሉ፣ ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት ገለጹ። በጥቃቱ ከሲቪሎች በተጨማሪ፣ የጤና ቢሮ ኃላፊ እና ባለሞያ፣ ፖሊስ እና የኦሮሚያ ክልል ሚሊሺያ አባላት እንደተገደሉ፣ የምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና አባያ ወረዳ የጸጥታ እና አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ አስታውቀዋል።


የአካባቢው ሰላም እና ጸጥታ ጥበቃም፣ ከወረዳው እና ከዞኑ አቅም በላይ እንደኾነ አክለው የገለጹት ኃላፊው፣ የፌደራል መንግሥቱን ጣልቃ ገብነት ጠይቀዋል።

ጥቃቱ ባስከተለው አለመረጋጋት የአካባቢው መደበኛ እንቅስቃሴ እንደተገደበም፣ የአሜሪካ ድምፅ ያነጋገራቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ለጥቃቱ ተጠያቂ ከተደረገው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ታጣቂዎች ቃል አቀባይ፣ ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።

(ዝርዝሩን ከተያያዘው የቪዲዮ ፋይል ያገኛሉ)

XS
SM
MD
LG