በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሦስት አገራት ኤኮዋስን ለቀው እንደወጡ አስታወቁ


ፋይል - የሳህል አገራት ጥምረትን የሚደግፉ ሰዎች በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒዠር ከኤኮዋስ በመውጣታቸው ደስታቸውን ሲገልፁ - ጥር 28፣ 2024
ፋይል - የሳህል አገራት ጥምረትን የሚደግፉ ሰዎች በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙ ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒዠር ከኤኮዋስ በመውጣታቸው ደስታቸውን ሲገልፁ - ጥር 28፣ 2024

በምዕራብ አፍሪካ የሚገኙት ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ እና ኒዠር ከቀጠናው የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኤኮዋስ) ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታውቀዋል። ኤኮዋስ በአገራቱ የተፈፀሙትን መፈንቅለ መንግስቶች ለመቀልበስ ሲል “ኢሰብዓዊ” ብለው የገለጹትን ማዕቀብ ጥሏል ሲሉ የአገራቱ ሁንታዎች ትናንት እሁድ በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በሦስቱም አገራት ብሔራዊ ቴሌቭዥኖች በተነበበው መግለጫ፣ ከኤኮዋስ እና ከማዕከላዊ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ (ኢካስ) መልቀቃቸውን አስታውቀዋል። ሦስቱ አገራት በመግለጫቸው፣ ኤኮዋስ ከመሥራቾቹ የቀድሞ አባቶች እንዲሁም ከፓን አፍሪካዊ ሃሳቦች አፈንግጧል ሲሉ ከሰዋል።

“በውጪ ኃይሎች ተጽእኖ፣ ኤኮዋስ የተመሠረተባቸውን መርሆች በመተዉ፣ ለዓባል አገራት ሥጋት ሆኗል” ብሏል መግለጫው።

በአካባቢው እንደ ፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ባለሥልጣን የሚታየው እና 15 ዓባላት ያሉት ኤኮዋስ፣ የኢኮኖሚ ትስስርን ለመፍጠር እ.አ.አ በ1975 የተመሠረተ ሲሆን፣ በቀጠናው በተከታታይ የተካሄዱትን መፈንቅለ መንግስቶች ለማቆም አቅም ማጣቱ ተነግሯል።

የአገራቱ ኤኮዋስን ለቅቆ መውጣት በምን ዓይነት ሂደት እንደሚፈፀም ግልጽ አይደለም ሲል የአሶስዬትድ ዘገባ አመልክቷል። የዜና ወኪሉ ላቀረበለት ጥያቄ ኤኮዋስ ወዲያውኑ መልስ ባይሰጥም፣ እውቅና የሚሰጠው ዲሞክራሲያዊ ለሆኑ መንግስታት ብቻ መሆኑን ከዚህ በፊት አስታውቋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG