በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ከሀማስ ጋር አብረዋል በተባሉ ሰራተኞቹ ዙሪያ አስቸኳይ ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ 


ምስሉ ጎብኚዎች በእየሩሳሌም በሚገኘው ብሄራዊ ቤተ መፃህፍት ውስጥ በግዙፉ ማሳያ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 የሃማስ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ወቅት የተገደሉትን የእስራኤላውያንን ፎቶግራፎች ሲመለከቱ ያሳያል ።
ምስሉ ጎብኚዎች በእየሩሳሌም በሚገኘው ብሄራዊ ቤተ መፃህፍት ውስጥ በግዙፉ ማሳያ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 የሃማስ ታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት ወቅት የተገደሉትን የእስራኤላውያንን ፎቶግራፎች ሲመለከቱ ያሳያል ።

የፍልስጤም ስደተኞችን የሚረዳው የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ተቋም (UNRWA ) 12 ሰራተኞች ፣ ሀማስ በእስራኤል ላይ ባደረሰው የጥቅምት 7ቱ የሽብር ጥቃት ላይ ተሳትፈዋል የሚለውን ውንጀላ ተከትሎ ፣ የተመድ ዋና ጸሓፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በድርጅቱ የውስጥ ቁጥጥር አገልግሎት በኩል አስቸኳይ ምርመራ እንደተጀመረ በዛሬ ዕለት አስታውቀዋል ።

የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ተቋም የበላይ ኀላፊ የሆኑት ፊሊፕ ላዛሪኒ ክስ የቀረበባቸውን 9 ሰራተኞች በአስቸኳይ በመለየት ከስራ እንዲታገዱ እንዳደረጉ ጉቴሬዥ ተናግረዋል ። አንደኛው ሰራተኛ ሞሞታቸው ሲረጋገጥ የሌሎች ሁለት ሰራተኞች ማንነት እየተጣራ እንደሆነም ዋና ጸሃፊው አክለዋል።

ማንኛውም በሽብር ተግባራት ላይ ተሳታፊ የሆነ የድርጅታቸው ሰራተኛ የወንጀል ክስን ጨምሮ ተጠያቂ እንደሚሆን የተናገሩት ጉቴሬዥ ፣ተቋማቸው በመደበኛ አሰራሩ መሰረት ግለሰቦችን ለመክሰስ ብቃት ካለው ባለስልጣን ጋር ለመተባበር ዝግጁ እንደሆነም ገልጸዋል።

በአውሮፓዊያኑ ጥር 17 የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ተቋም ሙሉ እና ነጻ ድርጅታዊ ምርመራ እንደሚያደርግ ማስታወቁን ጉተሬዥ አውስተዋል ።

በውንጀላው ማግስት ለድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ ማድረጋቸውን ያቆሙ ሀገራት ፣ የዕለት ህልውናቸው ከድርጅቱ ድጋፍ ላስተሳሰሩ 2 ሚሊየን የጋዛ ሰላማዊ ሰዎች እና ለሰብአዊ ሰራተኞች በጣም አደገኛ በሆኑ አንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ ሲሰሩ መቆየታቸውን ለተናገሩላቸው በ10ሺዎች ለሚቆጠሩ ወንድ እና ሴት ሰራተኞች ዳግም የድጋፍ እጃቸውን እንዲዘረጉ ዋና ጸሓፊው ተማጽነዋል ።

የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ በትናንትናው ዕለት የተባበሩት መንግስታት የእርዳታ እና ሰብዓዊ ተግባራት ተቋም ለእውነተኛ ሰላም እና ልማት ዝግጁ በሆኑ ተቋማት እንዲተካ ጥሪ አቅርበዋል።

ካትዝ በማህበራዊ ሚዲያ መልዕክታቸው ላይ ሀገራት የአሜሪካን፣ አውስትራሊያን፣ ካናዳን፣ ብሪታኒያን፣ ጣሊያንን እና ፊንላንድን ፈለግ ተከትለው ለተቋሙ የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ እንዲያቆሙ ጠይቀዋል ።
እስካሁን ዘጠኝ ሀገራት ለተቋሙ የሚሰጡትን የገንዘብ ድጋፍ አቁመዋል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG