በአፍሪካ ጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን፣ በናይጄሪያ ከፕሬዚዳንት ቦላ ቲኑቡ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዬሱፍ ማይታማ ጋራ ተወያይተዋል፡፡
ናይጄሪያ ከሰሐራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ትልቁን የሕዝብ ብዛት እና ምጣኔ ሀብት የያዘች ሀገር ናት።
ብሊንከን የአራት አፍሪካ ሀገራት ጉብኝታቸውን እያደረጉ ያሉት የምዕራብ አፍሪካ ሣህል ቀጣና ያለመረጋጋት ስጋት በደቀነበት በዚህ ወቅት ነው። ማሊ፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ጊኒ እና ኒዠር ውስጥ ከሁለት ዓመት ወዲህ በርካታ የመንግሥት ግልበጣዎች መካሔዳቸውን ተከትሎ፣ የአካባቢው ጸጥታ ጉዳይ አሳሳቢ ሆኗል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ብሊንከን ጉብኝታቸውን በመቀጠል ወደ አንጎላ ይጓዛሉ።
ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ያገኛሉ፡፡